ውድድሩን የሚመሩ ዋና ዋና ደንቦች በሚከተለው መልኩ ቀርበዋል፦
- የተሳታፊዎች ብቃት፦ ውድድሩ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የይዘት ፈጣሪዎች ብቻ ክፍት ሲሆን፣ ተሳታፊው በቲክ ቶክ አካውንቱ ቢያንስ 10,000 ተከታይ ሊኖረው ይገባል ።
- የምዝገባ ግዴታ፦ ተሳታፊዎች በቅድሚያ winnerherbal.com/#winnerGregistration ላይ መመዝገብ አለባቸው ። ሳይመዘገቡ ቪዲዮ መለጠፍ ከውድድር ውጪ ያደርጋል ።
- የቪዲዮ መስፈርቶች፦
- ርዝመት፦ ከ30 ሰከንድ ጀምሮ።
- ኦሪጅናሊቲ፦ ቪዲዮው የራስ ፈጠራ መሆን አለበት፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ ቪዲዮ ወዲያውኑ ውድቅ ይደረጋል ።
- ሃሽታግ እና ታግ፦ የግድ #WinnerGlowChallenge ሃሽታግን መጠቀም እና @WinnerHerbal የሚለውን አካውንት ሜንሽን ማድረግ ግዴታ ነው ።
- ሊንክ፦ በቪዲዮው መግለጫ (caption) ወይም ባዮ (bio) ላይ https://winnerherbal.com/ የሚለውን ሊንክ ማካተት ያስፈልጋል ።
የሚመከሩ እና የማይፈቀዱ ተግባራት (Do’s & Don’ts)
|
የሚመከሩ (Do’s) |
የማይፈቀዱ (Don’ts) |
|
ምርቶችን በቪዲዮው ላይ በግልጽ ማሳየት |
ያልተረጋገጡ የህክምና መረጃዎችን መስጠት |
|
ፈጠራ የታከለበት ይዘት (ዳንስ፣ ኮሜዲ፣ ወዘተ) |
ድርጅቱን የሚያሳንሱ አሉታዊ ይዘቶች |
|
ጥራት ያለው ብርሃን እና ድምጽ መጠቀም |
በሌላ ሰው ቪዲዮ መሳተፍ (Originality) |
የማሸነፊያ መስፈርቶች (Scoring Matrix)
አሸናፊዎች የሚመረጡት በሁለት ደረጃዎች ሲሆን፣ በመጀመሪያ ነጥብ ይሰበሰባል፤ በመቀጠል ደንብ መከበሩ ይረጋገጣል ።
- እይታ (Views & Reach): 30 ነጥብ
- ተሳትፎ (Engagement): 30 ነጥብ ሼር፣ላይክ፡ቬቨራይት
- ጥራት (Quality & Editing): 10 ነጥብ
- ብራንድ ተገቢነት እና ፈጠራ (Brand Relevance and Creativity): 25 ነጥብ
- ደንብ ማክበር (Formality): 5 ነጥብ
ማስጠንቀቂያ፦ ሃሽታግ፣ ታግ ወይም ሊንክ ከጎደለ ከጠቅላላ ነጥብ ላይ 50% ቅጣት (Penalty) ይዳርጋል ።
የሽልማት መጠን (Prize Pool)
ለዚህ ውድድር በአጠቃላይ 500,000 ብር ተመድቧል፦
- 1ኛ ደረጃ፦ 300,000 ብር
- 2ኛ ደረጃ፦ 150,000 ብር
- 3ኛ ደረጃ፦ 50,000 ብር